አዛርባጃን25 ዓመታትን በነጻነት ጎዳና

olympics
የስፖርት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን አትሌቶቿ በሚያስመዘግቡት ድልምአዛርባጃን የስፖርት ኃያል መሆኗን ያሳያሉ

በቅርቡ በብራዚሏ መዲና ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር በነጻነት ጉዞ ሩብ ምዕተ-ዓመትን ያስቆጠረችው አዛርባጃን በአምሥት የውድድር ዓይነቶች 18 ሜዳሊያዎችን ለማግኘት በቅታለች፡፡ በካስፒያን ባሕር እና በኮከሰስ ትልቋ ከተማ የሆነችው ባኩ የአዛርባጃን መዲና ከመሆን አልፋ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ጫወታዎች ባለፈው ዓመት አስተናግዳለች፡፡ ስፖርት እንደሚታወቀው በግል እና በጋራ ጥረት (ማለትም በኮርፖሬትም ሆነ በመንግሥት ደረጃ በሚደረጉ ጥረቶች) የተገኘ ስኬት ማንጸባረቂያ መድረክ ነው፡፡ አዛርባጃን ም ብትሆን በትልልቅ ስፖርታዊ መድረኮች ላይ የተቀዳጀችው ስኬት ቀደም ሲልም በዓለም ዓቀፍ ፖለቲካዊ መስኮች ያገኘቻቸው እመርታዎች እና የማኅበረ-ኢኮኖሚ ዕድገቷ ነጸብራቅ ነው፡፡ የሩብ ምዕተ-ዓመቱ እመርታ 1) ሀገሪቱ የዓለምን ገበያ ልትቀላቀል የቻለችበትን ዕድል የፈጠሩት እና ዘይት እና ጋዝ ያስገኙት የዋና ዋና የኃይል አቅርቦቱ ኢንደስትሪ ፕሮጀክቶች 2) የኢኮኖሚ ለውጦች እና ግለሰባዊ የንግድ ስኬቶች 3) በኢኮኖሚ እና የሕዝብ አስተዳደር መስኮች የታዩ አዲስ ቴክኖሎጂዎች 4) የማኅበረሰብ ባሕሎች መዳበር 5) የመጀመሪያዎቹ ሀገሪቱ የታወቀችባቸው ምርቶች 6) በሥልጣን ክፍፍል ላይ የመጣው ዓይነታዊ ለውጥ እና 7) መንግሥት ሀገሪቱ በተያያዘችው የዝመና ሂደት ዋንኛ አንቀሳቃሽ የመሆኑት ውጤት ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ግን የአንድ መሠረታዊ ሂደት---አዛርባጃን ከቀድሞው የሶቭዬት ማኅበረሰብ ተነጥላ በነጻነት መውጣቷ እና በአህጉራዊም ሆነ ዓለምዓቀፋዊ ፖለቲካ ጉልህ ሚና እየተጫወተች የመምጣቷ--መገለጫ ነው፡፡

አዛርባጃናውያን በዚህ ሩብ ምዕተ-ዓመት ጊዜ ውስጥ በሀገር እና ማኅበረሰብ ግንባታ ትልቅ እመርታን አሳይተዋል፡፡ ምናልባት በታሪክ እንደምናውቀው በ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ እንደነበረው ያህል የሚባልለት የሀገር እና ማኅበረሰብ ግንባታ ነው ወይ የመጣው የሚለው ሊያጠያይቅ ይችል ይሆናል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የመጀመሪያው የሶቭዬት ሪፐብሊክ ከተመሠረተበት እኤአ 1918-20 በሔይዳር አሊዬቭ መሪነት በ 1970ዎቹ እስከተከናወነው የሶቪዬት ልማት ድረስ ያለውን ጊዜ በታሪክ ተወራራሽነትም እንዲሁም በሀገራዊ ትውስታ አንስተን በመመልከት ከዚህ አንጻር የዛሬዋን አዛርባጃን ብንመዝናት ሀገሪቱ ከመረሳት ይልቅ ወደ አንድ ብሔራዊ ልማት ሂደት ማምራቷን እንገነዘባለን፡፡

በእነዚህ የነጻነት ትሩፋቶች ለሕዝብ መዳረስ በጀመረባቸው ዓመታት በተለያዩ መስኮች ዕድገቶች ተመዝግበዋል፡፡ የመረጃ መገናኛ ቴክኖሎጂ (አይ. ሲ. ቲ.) ኩባንያዎች ተመስርተው እያደጉ ሄደዋል፤ የሸማቹ ዘርፍ ተመንድጓል (የመኪና ገበያውን እና ሪል ስቴቱን ማንሳት ይቻላል)፤ እንዲሁም አዳዲስ ቢዝነሶች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቅ ብቅ ብለዋል፡፡ በዚህ የ አዛርባጃንድራት ሌላው ትልቅ ዋጋ አለው ተብሎ የሚጠቀሰው በዓለምዓቀፍ የትራንስፖርት ኮሪደሮች ውስጥ ሀገሪቱ እንድትቀላቀል ያስቻለው አዲሱ የትራንስፖርት መሠረተ-ልማት ነው፡፡ ትላልቅ እና ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች እና ዘመናዊ አውራ-መንገዶች መገንባታቸው የከተሞችን ገጽታ ከመቀየሩም በላይ የክፍለሀተ-ሀገራትን የቆየ የኢኮኖሚ ምስል ቀይሯል፡፡ አዛርባጃን ዛሬ ዛሬ የዓለም ዓቀፍ የሎጂስቲክስ እምብርት ሆናለች፡፡ ከባኩ ሌላ በሀገሪቱ ሌሎች ስድስት የአየር ማረፊያዎች ያሉ ሲሆን ዋንኛው የሀገሪቱ የአየር መንገድ (AZAL) የደቡብ ኮከሰስን ከሁሉም የተቀሩት የዓለም ክፍሎች ጋር የሚያገናኝ ቁልፍ የክፍለ-አህጉሩ የአየር ትራንስፖርት አቅራቢ ለመሆን የቻለ ነው (በቅርቡ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በጋራ የአቪዬሽን ክልል ዙሪያ ስምምነት ይፈጽማል ተብሎ ይጠበቃል)፡፡ እኤአ ከ 2000 ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ከመጣው የመረጃ መረብ (ኢንተርኔት) እና የዋና እና የማኅበራዊ የሕዝብ መገናኛ ብዙሀን በመረጃ አቅራቢነት መፍለቃቸውን ከእነዚህ ላይ አክለን ስንመለከተው ሥዕሉን እጅግ ያጎላዋል፡፡

airport
ዘመኑ የሚጠይቃቸውን ፍላጎቶች እና የተለጠጡ ጥያቄዎችን የሚያሟላው እና አዲሱ የባኩ ዓለምአቀፍ አየርማረፊያ

አዛርባጃንድራት ምጣኔ-ሀብት፡ እኤአ ከ 2003 እስከ 2007 ባሉት ሶስት ዓመታት ውስጥ የአዛርባጃን ኢኮኖሚ ወደ 96 በመቶ በጣም ቀረብ ባለ አሀዝ ያደገ ሲሆን ይኼ በደቡብ ኮከሰስ አቻ የሌለው ዕድገት ነበር፡፡ በ 2007 የአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ.) ዕድገት (በዓመት ከ 22 በመቶ በላይ ነበር) በኮመንዌልዝ ኦፍ ኢንዲፔንደንት ስቴትስ ወይንም ሲ. አይ. ኤስ. ትልቁ፤ በዓለም ደግሞ የመሪነትን ሥፍራ ከያዙት ተርታ የሚመደብ ነበር፡፡ እንደ ሲ.አይ.ኤስ. ኢንተርስቴት ስታቲስቲካል ኮሚቲ ከሆነ ከ 2003 እስከ 2007 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የአዛርባጃን ጂ.ዲ.ፒ. በ 3.17 እጥፍ ያህል ነው ያደገው፡፡ ሩሲያ በዚህ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ጂ.ዲ.ፒ.ዋ በ 1.5 እጥፍ ነው የጨመረው፤ የካዛኪስታን ደግሞ ሁለት እጥፍ ነው የዓለም ባንክ እና የዓለምዓቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይ.ኤፍ.ሲ.) በ 2009 ቢዝነስ ላይ ባወጡት ሪፖርት አዛርባጃን ለውጦችን በመተግባር ከዓለም ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በዚህ ሪፖርት የመንግሥት ደምብ የቱን ያህል ለአነስተኛ እና መካከለኛ ቢዝነሶች የተመቸ እንደነበረ ነው የታየው፡፡ በአመልካችነት ሁለቱ ግዙፍ የዓለምዓቀፍ የገንዘብ ተቋማት ካስቀመጧቸው 10 መለኪያዎች ሰባት ያህሉ የተሻሻሉ ሲሆን ሀገሪቱም ቀደም ሲል ከተቀመጠችበትበ 64 ደረጃዎች ያህል ራሷን በማሻሻል በ 33ኛ ደረጃ ላይ ደቡብ አፍሪካን፤ ፈረንሣይን እና እስራኤልን ትከተላለች፡፡ የነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ገቢ ማሽቆልቆል ቢያጋጥማትም በ 2015 የዳቮስ የኢኮኖሚ ፎረም በ 2015 ባወጣው የግሎባል ኮምፔቲቲቭነስ መለኪያ መሠረት ከሲ.አይ.ኤስ ሀገራት ሁሉ ቀዳሚ መሆን የቻለች ሲሆን ከዓለም ደግሞ 40ኛ ሥፍራን ይዛለች፡፡

ሃይደር አሊየቭ ማእከል
ሃይደር አሊየቭ ማእከል

በ 20 የነጻነት ዓመታት ወቅት በአዛርባጃን ኢኮኖሚ ከ 100 ቢልዮን ዶላር ያላነሰ ገንዘብ ኢንቬስት የተደረገ ሲሆን ይኼም ሀገሪቱ ለልማት እንቅስቃሴዎች የቱን ያህል ምቹ የሆነ ሁኔታ መፍጠሯን በግልጽ ያመላክታል፡፡ በዚህ ረገድ ልናስገነዝበው የሚገባ ነጥብ ቢኖር የአዛርባጃን የሀገር ውስጥ የኢንቬስትመንት እንቅስቃሴዎች እ. ኤ. አ. በ 2000 ላይ ከአጠቃላዩ ኢንቬስትመንት 47.5 በመቶ የሚሆነውን ሲይዙ እ.ኤ.አ. በ 2010 ማብቂያ ደግሞ ይህ ቁጥር አሻቅቦ 75.7 በመቶ መድረሱ ነው፡፡ ይኼም በ 10 ዓመት ውስጥ 16.3 ያህል ጊዜ ጭማሪ እንደሆነ ማመልከት ይቻላል፡፡ በመሆኑም በአዛርባጃን ገንዘብ ለብሔራዊው ኢኮኖሚ ዕድገት የሚውል እንጂ እምብዛም ወደ ውጭ የሚወጣ አይደለም፡፡ ባለፉት 10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የኢንቬስትመንት መጠን 4.7 ጊዜ ያህል ነው ያደገው፡፡ በዚህ በተጠቀሰው ጊዜ ውጥ የአውሮፓ ኅብረት አባል ሀገራትን የሚወክሉ ባለሀብቶችና ኩባንያዎች በሀገሪቱ ወደ 20 ቢልዮን ዶላር የሚሆን ቋሚ ካፒታል ፈሰስ አድርገዋል፡፡

stadium
በማታ የሚነሱ ፎቶግራፎች በሪፐብሊኳ ከተሞች ያሉ ለውጦችን በደንብ ያሳያሉ። ባኩ ውስጥ ከሚገኘው የኦሎምፒክ ስታዲየም አጠገብ የሚገኝ ማሳለጫ ፎቶ

ባለፉት 10 ዓመታት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ቀውሶች ቢከሰቱም በአፍጋኒስታን ዓመታዊ ኢንቬስትመንት ከ 12 እስከ 16 ቢልዮን ዶላር ባለው ውስጥ ይገመታል፡፡ ይኼም ከሃይድሮ-ካርቦን እና ማቀነባበሪያ ኢንደስትሪ ተመስቶ በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ ወዳልተመሠረቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያመራ መሆኑን መጥቀስ ይቻላል፡፡ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር ትንበያ ከሆነ በ 2016 በአጠቃላይ ኢንቬስት ከሚደረገው ውስጥ 40.3 በመቶ ያህል የሚሆነው ከነዳጅ ዘይት ምርት ውጭ ባሉ ዘርፎች ላይ ነው የሚሆነው፡፡ የውጭ ኢንቬስትመንትን ከነዳጅ ዘይት ውጭ ባሉ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ እንዲውል በማድረግ ነው የአዛርባጃን የኢኮኖሚ ልማት ጽንሰ-ሀሳብ የሚመሠረተው፡፡ መንግሥት በበኩሉ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ከነዳጅ ዘይት ውጭ ባሉ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያለውን አጠቃላይ ምርት (ጂ.ዲ.ፒ.) በእጥፍ ማሳደግ ይፈልጋል፡፡ የውጭ ኢንቬስትመንትን ለመሳብ ከሚያስችሉ ግብዓቶች አንዱ የታክስ ማሻሻያ ማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት በቅርቡ ይፋ ያደረጉት የታክስ ማሻሻያ ሀገሪቱን በቀጥታ ወደ ምዕራባውያን የታክስ ደረጃ የሚያሸጋግር ሲሆን በዚህ ሥርዓት መሠረት ታክስ እና የጉምሩክ ክፍያዎች የመንግሥት ዋንኛ የገቢ ምንጮች ይሆናሉ፡፡

የአዛርባጃን ዓለም ዓቀፋዊ መታወቂያ ዓርማዎች፡ ያለፉት 25 የነጻነት ዓመታት ሕዝቡ በመንግሥት እና ኮርፖሬት ተቋማት እገዛ የሀገሪቱን እምቅ ሀብቶች በመጠቀም ልዩ የሆነ የሀገሪቱ መለያ ምልከት ይፈጥር ዘንድ አስችለዋል፡፡ የሀገር መለያ መፍጠር ወይንም ደግሞ የቱሪዝም ኢንደስትሪው ዕድገት ላይ ተጽዕኖ ያለው፤ የውጭ ኢንቬስተሮችን ለመሳብ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ስለ ሀገሪቱ የሚባለውን ለመወሰን የሚያስችል አዎንታዊ ገጽታን መፍጠር የተወሳሰበ እና ከባድ ሂደት ነው፡፡ እንደ ብሔራዊ እሴቶች፤ የተለዩ መልከዓ-ምድራዊ ባሕሪያት፤ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፤ ፖለቲካዊ እና ማኀበራዊ ሂደቶች፤ የብሔር እና ባሕሎች ገጽታ፤ ባሕሎች፤ ወጎች እና ሥርዓቶች ያሉትን ይጠይቃል፡፡

rocket
አዛርባጃን የራሷን ሰው ሰራሽ ሳተላይት ማምጠቋ ከህዋ ኃያላን መካከል አንዷ እንድትሆን አስችሏታል

በመሆኑም አዛርባጃን ም ልክ እንደ ሌሎች በርካታ ሀገራት ሁሉ ለቢዝነስ እና ኢንቬስትመንት ምቹ እንደሆነች ሀገር፤ በተለያዩ ሥልጠኔዎች መካከል ለሚደረግ ዓለምዓቀፋዊ መስተጋብር ማዕከል መሆኗን፤ በዓለም የሳይንስ፤ የባሕል እና የሃይማኖት ልሂቃን መካከል ለሚደረግ ነጻ መስተጋብርም እንደ ጥሩ መድረክ ሆና ማገልገሏን፤ ማራኪ ብዝሀነትን የምታንጸባርቅ የቱሪስት መዳረሻ፤ እንደ ጥሩ የኃይል ጥሬ ዕቃዎች እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የግብርና ውጤቶች አቅራቢ አድርጋ ራሷን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቬስተሮች ታቀርባለች፡፡

በመሆኑም የአዛርባጃን ን ባሕል፤ ሪሶርስ እና ኢኮኖሚ ከላይ በቀረበው ዓይነት ከተመለከትነው የሚታወቁ ዓለምዓቀፍ መለያዎችን ወይንም ወደ መለያነት እየደረሱ ያሉ የተለያዩ መገለጫዎችን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡

አዛርባጃን በታሪክ የነዳጅ ዘይትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለንግድ ያቀረበች ሀገር ናት ማለት ይቻላል፡፡ በጥልቅ ውሃ ውስጥ የሚገኘውን እና ጥራት ያለውን የአዛርባጃን የነዳጅ ዘይትን የሚወክለው አዘሪ ላይት በዓለም ዓቀፉ ገበያ የሀገሪቱ መለያ ምርት ለመሆን በቅቷል፡፡ ከዚህ ዓይነቱ ዘይት የሚመረተው የአቪዬሽን ኬሮሲን በተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ግምት እና ቦታ የተሰጠው ነው፡፡ ይህ ምርት በአዳዲስ የሀገሪቱ የዘይት እና ፔትሮ-ኬሚካል ማጣሪያዎችም መመረቱ ይቀጥላል፡፡

አዛርባጃን ምንም እንኳ በልዩ የእስልምና ባሕሏ የምትታወቅ ትሁን እንጂ አዳዲስ ሀሳቦችን ለመቀበል የሚያስችል ብዝሀነት አላት፡፡ አዛርባጃን ተሞክሮዋን እና ባሕሏን በታቀደ እና በታሰበበት መልኩ ለውጭው ዓለም በማቅረብ በምሥራቁ እና በምዕራቡ መካከል መቀራረብን ይፈጥራል የተባለ ይፋዊ ያልሆነ ማኅበረ-ፖለቲካዊ መለያ መፍጠርም ችላለች፡፡ መዲናዋ ባኩ የስመ-ጥሩ እና ቀዳሚው አዛርባጃን መለያ ስም (አየር መንገድ) መናኸሪያ ናት፡፡ በዚህች ከተማ ውስጥ ልዩ የሆኑ የኪነ-ሕንጻ ውበቶችና ታሪካዊ ቅርሶች ያሉ ሲሆን የሕዝቡ እንግዳ ተቀባይነት እና በብዝሀነት መካከል የሚታየው አብሮነትና መቻቻልም በባሕል እና ዘመናዊነት መካከል ያለውን ጤናማ መስተጋብር ያመለክታል፡፡

ኮምዩኒኬሽን ዘመናዊ መደረጉ የተለያዩ ስኬታማ የአዛርባጃን ኩባንያዎች በመረጃ ቴክኖሎጂ (አይ.ቲ.) ዘርፍ ብቅ ብቅ እንዲሉ መንገድ ከፍቷል፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለምሥራቅ አውሮፓ፤ ኤሽያ እና ደቡብ አሜሪካ ያቀርባሉ፡፡

በግብርናው መስክ የተደረገው የዝመና ለውጥ እና የማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማት መርሀ-ግብሮች የተለያዩ የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ኩባንያዎች እንዲፈጠሩ መንስዔ ሆነዋል፡፡ የአዛርባጃን pomerante በሩሲያ በስፋት የታወቀ እና የሚዘወተር መለያ ስም ሆኗል፡፡ Recall Naftalanደግሞ ከሶቪዬት ጊዜ ጀምሮ ለሕክምና የሚጠቅም ፍቱን ዘይት እና ስመ-ገናና የሀገሪቱ ምርት ሆኗል፡፡

port
በባሕር የሚተላለፈው የጭነት ብዛት በእጅጉ ጨምሯል

ብልሀት የተሞላበት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፤ ብዙ አቅጣጫዎችን ያማከለ የሀገር ውስጥ ፖሊሲ፤ እንደ ጊዜው እና ሁኔታዎች ራስን ለማስተካከል ያለ ፈቃደኝነት፤ መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሚተነበይ መሆን ይጠቀሳሉ፡፡ በዐሥር ዓመታት ጊዜ ውስጥ የአዛርባጃን ን ዋና ዋና መለያ ስሞችና ምርቶች (ምንም እንኳ በዓለም ዓቀፉ ገበያ ካለው ድርሻ አንጻር አነስተኛ ቢሆንም ወደ አውሮፓ ኅብረት የምትልከው ሃይድሮ-ካርቦን እና አውሮፓን እና ኤሽያን ማገናኘት የሚችል የመተላለፊያ ኮምዩኒኬሽን አሰራር) ማስተዋወቅ ተችሏል፡፡ በእነዚህ ሙሉ በሙሉ ኢኮኖሚያዊ በነበሩ መለያ ስሞችና ምርቶች ላይ ደግሞ በሀገሪቱ የሰፈነው ብዝሀነት እና የሃይማኖት መቻቻል እንደ ሌላ መታወቂያ ስም በመተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ አዛርባጃን ምንም እንኳ በተዛባ መልኩ የቀረቡ ገጽታዎች ቢኖሯትም ታታሪነት የሚታይበት የማኅበረ-ኢኮኖሚ ልማት እና የውጭ ፖሊሲን በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡ በሲ.አይ.ኤስ. ውስጥ ምንም ዓይነት ከጥምረት የሚመነጭ ግዴታ ከማንም ጋር ካልገቡ እና ነጻነታቸውን ከጠበቁ በጣት የሚቆጠሩ ሀገራት አንዷ የሆነችው አዛርባጃን በብልሀት የውጭ ግንኙነቷን መምራት የምትችል ሀገር ናት፡፡

oild industry
በከፍተኛ ባሕር የሚገኙ የዘይት ሰራተኞች ከተማ በሆነችው ዝነኛዋ ኦይል ሮክስ ሥር ነቀል ለውጦች ተደርገዋል

የዚህ ስትራቴጂ አንዱ ምሳሌ እ. ኤ. አ. ነሐሴ 8፤ 2016 ላይ በመዲናዋ ባኩ በአዛርባጃን ፤ ሩሲያ እና ኢራን መካከል የተካሄደው የሶስትዮሽ ስብሰባ ሲሆን በዚህ ስብሰባም የኢኮኖሚ ትብብር ለማድረግ ስለሚቻልባቸው ዕድሎች እና ለበርካታ መጪ ዓመታት በመካከለኛው ምሥራቅ በብዙ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው የሚችል እንደ ሁኔታዎች እና ጊዜው ተለዋዋጭ የሆነ ክፍለ-አህጉራዊ መዋቅር ሊባል የሚችል የካስፒያን ‹ትሮይካ›ን ለመፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መሠረታዊ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ እዚህጋ ሊሰመርበት የሚገባው ትልቁ ነጥብ ቢኖር በባኩ፤ ተኼራን እና ሞስኮ መካከል ዋንኛው የስበት ማዕከልና የትብብር ትኩረት ኢኮኖሚው ሆኖ ከዚሁ ጎን ለጎን ግን ፖለቲካዊ ጥቅሞችም የሚታዩ መሆኑ ነው፡፡ በሶስቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ቅርርብ እና የጋራ መግባባት የተመለከቱ በርካታ ታዛቢዎች ቱርክንም ስብስቡ ውስጥ ስለ ማስገባት ያወሳሉ፡፡ በዚህ ረገድ ልንል የምንችለው ነገር ቢኖር ቱርክ (አንካራ) በምዕራባውያን ላይ ከነበራት ጥገኝነት እየተላቀቀች የሞስኮ-አንካራ-ተኼራን የንግድ እና ኢኮኖሚ ስብስብሊፈጠር የሚችል ሲሆን አዛርባጃን ደግሞ በዚህ ውስጥ የአገናኝነት ሚና ትጫወታለች፡፡

wind
ኢኮኖሚን ዘርፈ ብዙ በማድረግ ሂደት ውስጥ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች እየተፈጠሩ እና አማራጭ የኃይል ምንጮችም እያደጉ ነው

በዚሁ ዓመት በጸደዩ ወራት ባኩ አራተኛውን ግሎባል ፎረም ያስተናገደች ሲሆን ‹ወደ መድበለ-ዋልታ ዓለም የሚደረገው ግስጋሴ› የሚለው የፎረሙ መሪ ቃል ከመቼውም በላይ ከጊዜው እና ሁኔታዎች ጋር ያለው ተያያዥነት ሊጠቀስ ይገባዋል፡፡ ይህ ብዙ አቅጣጫዎችን ያማከለ እና መድበለ-ዋልታ ፖሊሲ ይኸው ዛሬ ዛሬ የበርካታ ሀገራት መገለጫ እየሆነ መጥቷል፡፡ በዚህ ረገድ ትልቅ የመሪነት ሚና የምትጫወተው አዛርባጃን ለረጅም ጊዜ የቆየ የጂኦ-ፖለቲካ የጥቅም ግጭት እንዲሁም አካባቢያዊ የብሔር ግጭቶች እና አለመረጋጋት በተጫጫነው ቀጠና ውስጥ ብትሆንም በርካታ አቅጣጫዎችን ማዕከል ያደረገ ፖሊሲን በመከተል ከሚታወቁ ጥቂት ሀገራት ተርታ ትመደባለች፡፡ በእርግጥ ምንም እንኳ የምዕራቡ ዓለም የማኅበራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ አስተዳደረዊ፤ ፖለቲካዊ እና የቴክኖሎጂ መሻሻል ምንጭ ቢሆንም በውጭ ተጽዕኖ ሥር የመውደቅ አደጋም እንዳለ መጠቆም ይገባል፡፡ አዛርባጃን እና ጎረቤት ኢራን ታሪካዊ እና ባሕላዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ቢሆኑም በተመሳሳይ ጊዜ ግን ፖለቲካዊ የአክራሪነት እስልምና ሊፈጠር የሚችልበት እምቅ-አቅም በሀገሪቱ (በኢራን) እንዳለ መረዳት ያሻል፡፡ ሩሲያከሁሉም የአካባቢው ሀገራት የበለጠ ደረጃ ላይ የምትቀመጥ እና ከባኩ ጋር የወታደራዊ-ፖለቲካዊ እና ሳይንሳዊ-ባሕላዊ ትብብር የምታደርግ አጋር ናት፡፡ ሩሲያ ምንም እንኳ በቁጥር ትልቁ የአዛርባጃን ዳያስፖራ ማኅበረሰብ የሚኖርባት ብትሆንም የሩሲያ የተጠናከረ ድጋፍ ለአርሜኒያ ብሔራዊ አማጺነት ትልቅ መንስዔ መሆኑ እና በዚህም የተነሳ የሬቫን ያራመደችው ፍጹም ለመታረቅ ፈቃደኛ ያልሆነ እና ግትር አቋም ለከረብካ ግጭት መባባስ ዓይነተኛ አስተዋፆ ማድረጉን ሳንጠቅስ ማለፍ የለብንም፡፡

ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ እዚህጋ ሌላው ልንጠቅሰው የምንችለው ጉዳይ አዛርባጃን በውጭ ፖሊሲዋ ሚዛናዊነትን ማበጀቷ በተለይም ለትንንሽ ወይንም መካከለኛ ሆነው ከኃያል ጎረቤት ሀገራት እና ዓለም ዓቀፋዊ ድርጅቶች (አጠያያቂ ውህደቶችን ጨምሮ ማለት ነው) በሚጣልባቸው ግዴታ ሸክም ውስጥ ለገቡ ሀገራት ጥሩ ተምሳሌት እና መማሪያ መሆኑን ነው፡፡

እስኪ አሁን ደግሞ የባኩን የአመራር ዘይቤ ምስጢር እንፈትሽ፡፡ የሀገሪቱ አመራር በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የውይይት ርዕስና አጀንዳ አድርጎ የአዲሷን ባኩ ጽንሰ-ሀሳብ ለውጭው ዓለም ማስተዋወቁ ጥሩ ስትራቴጂ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይህ ዓይነቱ ስትራቴጂ ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ ድርጅታዊ ጉዳት የሌለው ሲሆን ጥቅሞቹ ግን አያሌ ናቸው፡፡ በተለያዩ መስኮች (ከኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲ እስከ ባሕል እና ስፖርት ድረስ) ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ያገኙ አዛርባጃናውያንን በማሳተፍ በዓለም ዙሪያ የሚደረገው ፎረም የአዛርባጃን ን መለያ ምርቶች እና ስሞች ከፍ በማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ በጣም በርካታ ታዋቂ ሰዎችን (የቀድሞ እና አሁንም ያሉ የፖለቲካ ሰዎችን፤ ዓለምዓቀፍ ባለሥልጣናትን፤ ስመጥር ሳይንቲስቶችን እና የሚዲያ ሰዎችን) በእንዲህ ዓይነት ፎረሞች ላይ መጋበዝና ማሳተፍ ትልቅ የውጭ ሚዲያ ሽፋንን የሚስብ እና በተጋባዥ ሀገራት ልሂቃን ዘንድም በአዛርባጃን ላይ የረጅም ጊዜ ጥቅምን መሠረት ያደረገ ትስስር ለመፍጠር ፍላጎት እንዲዳብር በር ይከፍታል፡፡ ይህ ፍላጎት ከልሂቃኑ ቀስ በቀስ ወደ ተጋባዥ ሀገራት ሕዝብ ይወርዳል፡፡ የዚህ ውጤት ደግሞ ግልጽ ነው--የበርካታ ሀገራት ትላልቅ ባለሥልጣናት፤ ታዋቂ ሰዎች እና ቱሪስቶች ወደ አዛርባጃን ለጉብኝት ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ይመጣሉ፡፡ ነገር ግን ከምንም በላይ አዛርባጃን የገዛ ብሔራዊ ጥቅሞቿን (ዛሬ ላይ ትልቁ የአዛርባጃን እና የክፍለ-አህጉሩ ትልቁ የጸጥታ ችግር በሚባለው እና የአዛርባጃን መሬቶች በአርሜንያ መያዛቸውን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ) የሚጠብቁላት እውነተኛ ደጋፊ ለመሆን የበቁ አጋሮችን በእነዚህ 25 ዓመታት ጉዞዋ አግኝታለች፡፡ ይህ ትልቅ የፀጥታ ስጋትን የሚፈጥር ችግር ሊፈታ የሚችለው ግን አዛርባጃን እምብዛም ልትቆጣጠራቸው እና ተጽዕኖ ልታደርግባቸው በማትችላቸው ዓለም ዓቀፋዊ ጉዳዮች እና ሁኔታዎች ነው፡፡ የዚህ ፖሊሲ ዋንኛው ዓላማ ከግሎባላይዜሽን ትሩፋቶች መጠቀም ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ምሥራቅ እና ምዕራብን የማስተሳሰሩ ተልዕኮ በመንግሥት ፖሊሲ ውስጥ ከተካተቱት ከባሕል ብዝሀነት እና መቻቻል አንጻርም ሊቃኙ ይገባል፡፡

army
በወታደራዊ ዘርፉ ውስጥ ጥልቅ ተሃድሶ ተደርጓል

የዛሬዋ ጠንካራ አዛርባጃን የውጭ ግንኙነቷን የምታሰፋባቸውን አዳዲስ አድማair forcesሶች በመቃኘት ላይ ትገኛለች፡፡ ከዚህ አንጻር እንደ ገለልተኝነት ንቅናቄ፤ የእስልምና ትብብር ድርጅት እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅት ውስጥ ባሉት መዋቅሮች አባል መሆን አዳዲስ እና በተለያዩ አቅጣጫዎች እየሰፋ የሚሄድ የውጭ ጉዳይ መስክን ለማምጣት ይረዳል፡፡ እ.ኤ.አ. ከ 2013 ጀምሮ የኤሽያ ሀገራት ለመጀመሪያ ጊዜ በአዛርባጃን የነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ኢንደስትሪ ላይ በመሳተፍ አውሮፓን በዚህ መስክ ተይዞ ከቆየው የበላይነቷ መንቀል ችለዋል፡፡ ቻይና በአዛርባጃን የኢንቬስትመንት እና ኢንዱስትሪ አጋሮች ዝርዝር ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ በተደጋጋሚ ስሟ እየሰፈረ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አዛርባጃን በቻይና አማካይነት በተጀመሩ እና በኤሽያ የንግድ እና ትራንስፖርት መሠረተ-ልማትን ለመገንባት በሚያግዙ ፕሮጀክቶች ውስጥም ተሳታፊ ናት፡፡ እነዚህ ፕሮጀክቶች ምሥራቅ እና ምዕራቡን በአዲስ መንገድ ያስተሳስራሉ፡፡ እርግጥ ነው በአዛርባጃን የኢኮኖሚ ትብብር እና የንግድ ተሳትፎ ካላቸው ሀገራት መካከል አውሮፓውያን---ማለትም ሩሲያ እና ቱርክ---አሁንም የበላይነቱን እንደያዙ ነው፡፡ ነገር ግን አዲስ የውጭ ኢኮኖሚያዊ ትብብሮችን ለማድረግ የሚያስችሉ ፍላጎቶች ከሌሎች ሀገራት እየመጡ እንደሆነ ምልክቶች ይታያሉ፡፡

በአሁን ሰዓት አዛርባጃን ያለ ምንም ማጋነን በክፍለ-አህጉሩ ኃያልነትን የተቀዳጀች ሀገር እንደሆነች ይሰማታል፡፡ ይኼም ሲባል የቀደመጀው እና የመካከለኛው ትውልድ አባላት ያኔ ሀገሪቱ የልዕለ-ኃያሏ ሶቪዬት ኅብረት አካል በነበረች ሰዓት የነበራት ዝና እና ኃይል አሁንም ከውስጣቸው ስለማይጠፋ አዛርባጃን ም እንደዚያ እንደሆነች አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ ያኔ ሶቪዬት ኅብረት ኃያል በነበረች ሰዓት በርካታ ዜጎቿ በወጭ ሀገራት በመስፈር ጠንካራ ዳያስፖራ ፈጥረዋልና ከእነዚህ ማኅበረሰቦች መካከል ብዙ አዘርባጃነውያን ስላሉበት እነሱም ያኔ የነበረውን የበላይነት እና በዓለም ዓቀፍ ጉዳዮች አዛርባጃን ትልቅ ቦታ እንዳላት አድርገው የማሰብ አዝማሚያ ይታይባቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በግሎባል ግንኙነት ሀገሪቷ ያላት ደረጃ ይበልጥ እንዲጎለብት የትምህርት ፖሊሲው የበኩሉን አስተዋጾ አድርጓል፡፡ ይህ ፖሊሲ በዓለም ፖለቲካ የታነጸ የልሂቃን ማኅበረሰብ መፍጠርን ነው በዋናነት ዓላማው ያደረገው፡፡ ዛሬ ላይ ከ 15,000 ያላነሱ የአዛርባጃን ዜጎች በውጭ ሀገራት እና አሉ በተባሉ የተለየዩ ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ተምረዋል፡፡ በዚህ ረገድ አዛርባጃን ከሕዝብ ብዛቷ አንጻር ከሩሲያም ሆነ ከካዛኪስታን በልጣ ሄዳለች፡፡

flag square
የሃገሪቱ ዋና ከተማ የሆነችው ባኩ እድገት ቀስ በቀስ መላ ባሕረ ሰላጤውን እየሸፈነ የሚገኘውን ዝነኛው ባኩ ቦውልቫርድ እንዲጨመር አድርጓል

የማኅበራዊ ለውጦች መሪዎች፡ በአዛርባጃን የማኅበረ-ፖለቲካው ነባራዊ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ከመቀየሩም ባሻገር ዘመናዊ የሥልጣን ተቋማትም ጭምር ዳብረዋል፡፡ ከዚህ አንጻር ኢ-ጋቨርንመንት በሚል መጠሪያው የሚታወቀው እና በመረጃ መረብ አሠራር ላይ የተመሠረተ የሕዝብ አገልግሎት አቅርቦት አንዱ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በሕዝብ አስተዳደር እና አገልግሎት አቅርቦት ጥራት ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተንጸባረቀ ይገኛል፡፡ በመንግሥት የዜጎች አገልግሎት እና ማኅበራዊ ፈጠራ ኤጀንሲ ሥር የሚተዳደረው ASAN xidmət አገልግሎት በመባል የሚታወቀው (የአዛርባጃን የአገልግሎት ግምገማ መረብ) መመሥረት ትልቅ እመርታ ነው፡፡ በማኅበራዊው መስክ ሌላው ፈጽሞ በቀላሉ ሊታይ የማይችለው የትምህርት ለውጡ ነው፡፡ በሩብ ምዕተ-ዓመቱ ጉዞ ውስጥ በየዘርፉ የተመዘገበውን ዕድገት እንውሰድ ቢባል ሁለቱ ብልጫን ይወስዳሉ፡፡

pipe1
የባኩ-ተብሊሲ-ሴይሁን የነዳጅ ዘይት መተላለፊያ ግንባታ

ለመሆኑ ግን ኤሌክትሮኒክ የሕዝባዊ አገልግሎት አቅርቦት ለምንድነው እንድ ትልቅ እመርታ እና ብሔራዊ ኩራት ምንጭ ተደርጎ የሚታየው? በሶቪየት ኅብረት ጊዜ የነበረው ትውልድ ይኼንን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ አዎ፤ በያኔው ዘመን አንድ አገልግሎትን ለማግኘት ሲባል ረጅም ሰልፍ ይዞ መጠበቅ እና ጊዜንም ማጥፋት ግድ ይል ነበር፡፡ በቀላሉ በምሳሌ አስደግፈን እናቅርብ ቢባል እንኳ የመኖሪያ ቤት ምዝገባ ማስረጃ ለማግኘት ወይንም ዘመድን ማስመዝገብ በራሱ አንድን የሥራ ቀን ማዋል የሚጠይቅ እና ዜጎችን የሚያጉላላ እንደነበረ ይታወሳል፡፡ ከሶቪዬት ኅብረት ሀገሪቱ ነጻ በወጣችባቸው ጊዜያት ደግሞ በእነዚህ ሕዝባዊ አገልግሎቶች ውስጥ የሚታየው የተጨናነቀ ሰልፍ ወይ መጉላላት እንዳለ ሆኖ በትራፊክ ጽ/ቤት፤ በገቢዎች እና በሌሎች ተመሳሳይ የሕዝባዊ አገልግሎት ተቋማት ሁኔታው ተበራከተ፡፡

ይኼ የተወሳሰበ እና የተጨናነቀ የመንግሥት ቢሮክራሲ በሶቪዬት ኅብረት ጥላ ሥር የነበሩ ሀገራት ሁሉ የወረሱት መስተካከል የሚፈልግ ችግር ነበር፡፡ በመሆኑም የዜጎችን ፍላጎት ለማርካት እነዚህን ችግሮች የምንቋቋምባቸው መንገዶች ተመሳሳይ ናቸው--ከዓይነት እስከ ይዘት ለውጥ ድረስ፡፡ በዚህ ረገድ አንድ ማስታወስ የሚገባን ጉዳይ ቢኖር በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማሻሻል ማድረግ ነበር መንግሥት የወሰደው የመጀመሪያው እርምጃ፡፡ ከዚህ አንጻር ቢሮዎችና አገልግሎቶችን ሳይመርጥ በሕዝባዊ አገልግሎት ተቋማት ላይ ሁሉ የሚደረግ ለውጥ እና ሕዝብ ለአንድ አገልግሎት ወደተለያዩ ቢሮዎች እንዲሄድ የሚያስገድዱ አሠራሮችን መቀየር ትልቅ ግምት ያገኘ እና በቂ ተደርጎ የተወሰደ ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በተጨማሪነት የሎጂስቲክስ ሁኔታዎችን ማሻሻልም የእርምጃው አካል ሆኖ ብቅ አለ፡፡ ለምሳሌም ያህል እ.ኤ.አ. ከ 1990ዎቹ መጨረሻ እስከ 2000ዎቹ መጀመሪያ ድረስ የቤት ኪራይ እና ውሃ፤ መብራት እና ስልክ ክፍያዎች በአንድ የመረጃ እና የክፍያ ማዕከል ውስጥ እንዲጠቃለሉ ተደረገ፡፡ በዚህ የሕዝባዊ አገልግሎቶችን በማዘመኑ ጥረት የመጨረሻው እና ትልቅ ግምት የሚሰጠው የለውጥ መገለጫ ደግሞ በመረጃ መረብ እና ኔትዎርኪንግ አሠራር የሚደገፈው የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል (መስኮት) ለማግኘት የሚያስችለው አሰራር ነው፡፡ ይህ አገልግሎት ቀደም ሲል በጠቀስነው ASAN ሥር የሚሰጥ ሲሆን በአንድ የአገልግሎት ማዕከላቱ በሙሉ በአንድ ስም የሚሰራ የኮምፒውተር አሰራርን ይጠቀማሉ፡፡

pipe
ኢኮኖሚን ዘርፈ ብዙ በማድረግ ሂደት ውስጥ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች እየተፈጠሩ እና አማራጭ የኃይል ምንጮችም እያደጉ ነው

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስፋፋትን እና የ ‹አንድ መስኮት› አሠራር መፈጠርን ተከትሎ በመንግሥት አገልግሎቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ግልጽነትን የተከተለ የቁጥጥር እና ክትትል ሥርዓት በመኖሩ አሁን አሁን የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የተቀላጠፈ አሰራር አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ሌላው ሊጠቀስ የሚገባው የሙስና፤ ቢሮክራሲያዊ ማነቆ እና መሰል እንቅፋቶችን ማስቀረት መቻሉ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ቀደም ሲል የተጠቀሰውን ASANን በመጠቀም የመንግሥት ኤጀንሲዎች እና የግል ኩባንያዎች ወደ 240 የሚጠጉ የኤሌክትሮኒክ አሠራርን የሚከተሉ አገልግሎቶችን ለሕዝብ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ (የልደት፤ ጋብቻ፤ ሞት ወዘተ. ማስረጃ ማግኘት)፤ መታወቂያ እና ፓስፖርት፤ መንጃ ፈቃድ ማስቀየር፤ የታክስ ክፍያ ወዘተ. ይጠቀሳሉ፡፡ በባንክ፤ ኢንሹራንስ፤ የምክር አገልግሎት እና ጤናን በመሳሰሉት አቅርቦቶች ላይ የተሰማሩ የግል ኩባንያዎችና ድርጅቶችም ይኼንን አሰራር ተከትለው አቅርቦታቸውን ዘመናዊ ማድረግ ችለዋል፡፡ በአንጻራዊነት አጭር በሚባል ጊዜ ውስጥ ASAN xidmətከፍተኛ ብቃትን እያሳየ እና በሕዝብ ዘንድም ተወዳጅነትን እያተረፈ ከመሄድም ባሻገር አዲሱ የአዛርባጃን መለያ አርማ እስከመሆን መድረሱ ላያስገርም ይችላል፡፡ እርግጥ ነው እንዲህ ዓይነት አሠራሮች በብዙ የዓለማችን ሀገራት ውስጥ እንዳሉ ቢታወቅም በአመዛኙ ግን ከመንግሥት አገልግሎቶች የሚዘሉ አይደሉም፡፡ ይህ የASAN xidmət ጽንሰ-ሀሳብ ከዚህም የላቀ ጥልቀት ያለው ሲሆን በተለያዩ የመንግሥት ኤጀንሲዎች አማካይነት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደ አንድ ማዕከል ለማምጣት ያስችላል፡፡ የዚህ ተሞክሮ ሕጋዊነት ደግሞ በዓለምዓቀፉ የኤክስፐርቶች ማኅበረሰብ የተረጋገጠ ነው፡፡

asan

ይህ አሠራር ከተለመደው የተጠቃሚ ማንነትን ለማወቅ የሚያስችሉ መረጃዎች ባሻገር ዲጂታል ፊርማም በጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ይኼ ዓይነቱ ፊርማ ከሀገር ውጭም የአሰራሩ መገለጫ ሆኗል፡፡ ለምሳሌም እንበልና አንድ በዚህ አሠራር የተካተተ አዘርባጃናዊ ነጋዴ ወደ ሌላ ሀገር ለሥራ ሄዶ አገልግሎት ለማግኘት ጊዜ፤ ጉልበት እና ገንዘቡን ከመከስከስ ይልቅ እዚሁ ሆኖ በኢንተርኔቱ አገልግሎት የሚፈልገውን ማሳካት የሚችል ሲሆን የሰነዶቹ ሕጋዊነት ላይ ምንም የሚመጣ ለውጥ አይኖርም፡፡ ይህ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ለደቡብ ኮከሰስ እና ሌሎች ሀገራትም በእውነት ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡ ይህ አሠራር መሠረታዊ ለውጥን ማምጣት የቻለ በመሆኑ ከጆርጂያ፤ ካዛኪስታን፤ ሕንድ እና ሌሎች ሀገራት አሰራሩን ለማስጠናት ጥያቄ እየቀረበ ይገኛል፡፡ በመሆኑም አዛርባጃን ASAN imzaን እንደ ተጨማሪ የሀገሪቱ መለያ ዓርማ አድርጋ ማቅረብ የጀመረች ሲሆን ባለፈው ዓመትም በአውሮፓ ፓርላማ የኤሌክትሮኒክ ፊርማን በተመለከተ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡ ይህ የአገልግሎት ጥራትን እና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በሀገሪቱ የተጀመረው የኢ-ጋቨርንመንት አሠራር በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ጥራት ያለው አገልግሎት ደረጃ ሆኖ ለመቅረብ የሚያስችል እምቅ-አቅም አለው፡፡

እስኪ አሁን ደግሞ ወደ ትምህርት መስኩ ለውጦችና አሰራሮች እንለፍ፡፡ እ.ኤ.አ. ከ 2004 እስከ 2005 ድረስ በዚህ መስክ ለውጦች የተደረጉ ሲሆን በዚህም መሠረት አዛርባጃን ስም እና ምስሏን ከፍ የሚያደርጉላትን የሁለተኛ እና የከፍተኛ ደረጃ የትምህርት ተቋማት በስፋት አገኘች፡፡

ada
አዳ ዩ ኒቨርሲቲ ከመላው ዓለም የመጡ ተማሪዎች ቤት ነው

እ. ኤ. አ. ከ 2005 እስከ 2016 ባሉት 11 ዓመታት ጊዜ ውስጥ መንግሥት ለትምህርት ዘርፉ የመደበው በጀት ከ 18 ቢልዮን ዶላር ያላነሰ ነው፡፡ ወደ 3.2 ቢልዮን ዶላር ያህል ወይንም 17.7 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከዚህ በጀት ውስጥ በትምህርት መስክ ለሚደረገው ኢንቬስትመንት የዋለ ነው፡፡ በአዛርባጃን የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ከ 47,000 በላይ ኮምፒውተሮች፤ ወደ 11,500 ላፕ-ቶፖች፤ 2,300 የኢንተርኔት ላፕ-ቶፖች እንዲሁም 5,100 ኤሌክትሮኒክ ቦርዶችና ሌሎች አስፈላጊ ቁሣቁሶችና ዘመናዊ መሣሪያዎች ከኢንተርኔት መስመር ጋር ቀርቦላቸዋል፡፡

በከፍተኛ እና ስፔሻላይዝድ ትምህርቶች ላይ ለውጥ የመጀመሪያው ውጤት (እ.ኤ.አ. 2009-13)፡ ጠቅለል ባለ መልኩ እንግለጸው ከተባለ የይዘት እና ቴክኖሎጂ ለውጦች መጥተዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ስፔሻላይዜሽኖች ከሥራ ገበያው ፍላጎት አንጻር ተቃኝተው ማስተካከያ ተደርጎባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ የመንግሥት የሙያ-ተኮር ትምህርት ኤጀንሲ ይኼንን ያስተባብራል፡፡ የዩኒቨርሲቲዎች መዋቅር እና የሚተዳደሩበት አሠራርም ዘመናዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት እንዲያስችላቸው ተብሎ የተቀየሰ ነው፡፡ በሀገር ውጭ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ግንኙነቶች እየተፈጠሩ ሲሆን በሀገር ውስጥም ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች  እና ትምህርት ቤቶች ላይ ተመሳሳይ ትስስሮች እንዲፈጠሩ ተደርጓል፡፡

በዚህ ረገድ በቅርቡ የተካሄደው ለውጥ የአዛርባጃን ዩኒቨርሲቲዎችን ደረጃ የመወሰን ሥራ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲዎቹ የደረጃ ቅደም ተከተልም እንዲወጣ ከዓለም ዓቀፍ ኤክስፐርቶች ላይ እየተሰራ ይገኛል፡፡ላይመቆጣጠሪያ ገልግሎቶች ማዕከላት መፈጠር ነው፡፡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚደረጉትን ሳይንሳዊ ምርምሮች--በተለይም በፔትሮ-ኬሚካል ኢንደስትሪ እና ሌሎች የሀገሪቱ የኢንደስትሪ መስኮች---ከማደራጀት አንጻር ስልታዊ አሠራር ተዘርግቷል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር በሀገር ገጽታ ላይ ያተኮረ የትምህርት ሥርዓት እየቀረፀ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት 2017 የሁለተኛ ደረጃው የ 12 ዓመት ሳይክል ትምህርት ይጀመራል፡፡

khinalig
የሃገሪቱ ስነ-ምህዳር፣ ኢትኖግራፊያዊ፣ ታሪካዊ፣ ስነ-ምግብ እንዲሁም ቱሪስት አቅም ወደር የለውም

የትምህርት ሥርዓቱ በአዛርባጃን ለሚደረገው ማኅበረ-ሰብዓዊ ለውጥ ጥሩ ማሳያ ነውpomgranate፡፡ በሀገሪቱ ታዋቂ የማስተማር እና የምርምር ሥራን የሚያቀላጥፉ እና በልሂቃን መካከል ጥሩ ትስስር የፈጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈጥረዋል፡፡ እነዚህም ኤ.ዲ.ኤ. ዩኒቨርሲቲ (ዲፕሎማቲክ አካዳሚ)፤ በፕሬዚዳንቱ የሚመራው ፐብሊክ አድሚንስትሬሽን አካዳሚ፤ የሎሞኖሶቭ ሞስኮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የባኩ ቅርንጫፍ፤ የመጀመሪያው ሴሼኖቭ ሞስኮ ስቴት ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ የአዛርባጃን ቅርንጫፍ፤ የባኩ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ትምህርት ቤት እንዲሁም የአዛርባጃን ስቴት ኢኮኖሚክ ዩኒቨርሲቲ ናቸው፡፡ የአዛርባጃን ስቴት ኢኮኖሚክ ዩኒቨርሲቲ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ 25,000 ዩኒቨርሲቲዎችን ደረጃ በሚያወጣው ዌቦሜትሪክስ የ 5,000ኛ ደረጃን በ 2015 እ.ኤ.አ. አግኝቷል፡፡

shekiተረጋጋ ልማት፤ የሕዝቡ ምርጫ ስለ አዛርባጃን የፖለቲካ ሥርዓት ጨርሰን እና አንድም ሳናስቀር መናገር እንችል ይሆን? የዚህ ምላሽ ገደብ-የለሽ ነው የሚሆነው፡፡ ሆኖም የፖለቲካ መደቡ ያለ ሲሆን ስለዚያ መናገር እንችላለን፡፡ አዛርባጃን ከታሪኳ አንጻር ጠንካራ እና ቅቡልነት ያለው መንግሥት ያስፈልጋታል፡፡ ይኼም ሲባል እንደ ደቡብ ኮከሰስ ባለ የቆዳ ስፋት ባለው እና በርካታ ፈተናዎች ያልተለዩትን ሥፍራ ለማስተዳደር የግድ እንዲህ ዓይነቱ መንግሥት ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም እንዲህ ዓይነቱ መንግሥት ሊፈጠር የሚችለው ሁሉም የመንግሥት ተቋማት የጊዜን ፈተና በብቃት መወጣት የሚችሉ ከሆነ፤ ማኅበረሰቡ እና ሕዝቡ የግልም ሆነ ብሔራዊ ስኬትን እንዲቀዳጁ የሚያስችሉ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት መልካም አጋጣሚን ሲፈጥሩ ብቻ ነው፡፡ እርግጥ ነው ባለፉት 25 ዓመታት ሀገሪቷ በርካታ የነጻነት ትሩፋቶች ተቋዳሽ ሆናለች፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን የኢኮኖሚው እምቅ-አቅሞች፤ አሁን ያለው ማኅበረ-ፖለቲካዊ አሠራርን ከዳር ማድረስ፤ በባሕል፤ በትምህርት እና በሳይንስ ያሉ አዎንታዊ አዝማሚያዎችን እና መገለጫዎችን ማጠናከርን የመሳሰሉት ግን ገና በሂደት የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ አዛርባጃን በልማቷ ፍጹም አዲስ ምዕራፍ ላይ የምትገኝ ሲሆን ይኼ ልማት ግቡን እንዲመታ ደግሞ ያላትን ምሁራዊ እና ቴክኒካዊ እምቅ-አቅም አሟጣ መጠቀም ይጠበቅባታል፡፡ ገና ከተመሠረተች ከሩብ ምዕተ-ዓመት በላይ ላልሆናት እንደ አዛርባጃን ላለች ሀገር ዘመናዊነት እና ስኬት ቀላል አይደሉም፡፡ ከዚህ በፊት ያልተኬደባቸውን አስቸጋሪ መንገዶች መሻገር ብሎም ደግሞ ከዚህ ቀደም የማይታወቁ ፈተናዎችን መጋፈጥ ግድ ይላል፡፡ ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ባለፉት 25 ዓመታት የታዩት ጅማሮዎችና የተገኙት ውጤቶች አበረታች ናቸው፡፡ አዛርባጃን እነዚህን ከፍተኛ ግቦች እንደምታሳካ እሙን ነው፡፡ አዛርባጃናውያን በጽናት እና በማሸነፍ ጠንካራ ወኔያቸው ይታወቃሉና፡፡