አዛርባጃን25 ዓመታትን በነጻነት ጎዳና

በቅርቡ በብራዚሏ መዲና ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድር በነጻነት ጉዞ ሩብ ምዕተ-ዓመትን ያስቆጠረችው አዛርባጃን በአምሥት የውድድር ዓይነቶች 18 ሜዳሊያዎችን ለማግኘት በቅታለች፡፡ በካስፒያን ባሕር እና በኮከሰስ ትልቋ ከተማ የሆነችው ባኩ የአዛርባጃን መዲና ከመሆን አልፋ የመጀመሪያውን የአውሮፓ ጫወታዎች ባለፈው ዓመት አስተናግዳለች፡፡ ስፖርት እንደሚታወቀው በግል እና በጋራ ጥረት (ማለትም በኮርፖሬትም ሆነ በመንግሥት ደረጃ በሚደረጉ ጥረቶች) የተገኘ ስኬት ማንጸባረቂያ መድረክ ነው፡፡ አዛርባጃን ም ብትሆን በትልልቅ ስፖርታዊ መድረኮች ላይ የተቀዳጀችው ስኬት ቀደም ሲልም በዓለም ዓቀፍ ፖለቲካዊ መስኮች ያገኘቻቸው እመርታዎች እና የማኅበረ-ኢኮኖሚ ዕድገቷ ነጸብራቅ ነው፡፡ የሩብ ምዕተ-ዓመቱ እመርታ 1) ሀገሪቱ የዓለምን ገበያ ልትቀላቀል የቻለችበትን ዕድል የፈጠሩት እና ዘይት እና ጋዝ ያስገኙት የዋና ዋና የኃይል አቅርቦቱ ኢንደስትሪ ፕሮጀክቶች 2) የኢኮኖሚ ለውጦች እና ግለሰባዊ የንግድ ስኬቶች 3) በኢኮኖሚ እና የሕዝብ አስተዳደር መስኮች የታዩ አዲስ ቴክኖሎጂዎች 4) የማኅበረሰብ ባሕሎች መዳበር 5) የመጀመሪያዎቹ ሀገሪቱ የታወቀችባቸው ምርቶች 6) በሥልጣን ክፍፍል ላይ የመጣው ዓይነታዊ ለውጥ እና 7) መንግሥት ሀገሪቱ በተያያዘችው የዝመና ሂደት ዋንኛ አንቀሳቃሽ የመሆኑት ውጤት ነው፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ ግን የአንድ መሠረታዊ ሂደት---አዛርባጃን ከቀድሞው የሶቭዬት ማኅበረሰብ ተነጥላ በነጻነት መውጣቷ እና በአህጉራዊም ሆነ ዓለምዓቀፋዊ ፖለቲካ ጉልህ ሚና እየተጫወተች የመምጣቷ--መገለጫ ነው፡፡